የኬንያው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጋር የሳይንስ ሙዚየምን ጎበኙ

በጉብኝታቸውም በሳይንስ ሙዚየም ለእይታ የቀረቡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ምርትና አገልግሎቶችን ተመልክተዋል፡፡ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ ለፕሬዝዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ  እና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የኢመደአን አውደ ርዕይ አስጎብኝተዋል፡፡
የኬንያው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ለይፋዊ የስራ ጉብኝ ዛሬ መስከረም 26/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።